ኢትዮጵያ ከታላላቅ ልጆቿ መካከል አንዱ የኾኑትን የአፋሩን ሱልጣን አሊሚራህ
ሐንፍሬን በሞት አጣች፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም ከትናንት በስቲያ በትውልድ ስፍራቸውና የሱልጣንነት መቀመጫቸው በነበረችው አሳይታ ከተማ ተፈጽሟል፡፡
የአፋር ብሔረሰብ መንፈሳዊና ባህላዊ ፖለቲካዊም መሪ የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ በቀዳማዊ አፄ ኃይሌ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት (1923-1967) ከፍተኛ ሥልጣን ከነበራቸው መካከል አንዱ ነበሩ፡፡
በአፄ ኃይለ ሥላሴ የቢትወደድ ማዕርግ የተሰጣቸው ሱልጣን አሊሚራህ የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግሥትን በመቃወም በስደት በሳዑዲ ዓረቢያ በመኖር የአፋር ነፃ አውጭ ግንባርን Continue reading »