የሱልጣን ቢትወደድ አሊሚራህ ሥርዓተ ቀብር በአሳይታ ተፈጸመ

ኢትዮጵያ ከታላላቅ ልጆቿ መካከል አንዱ የኾኑትን የአፋሩን ሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬን በሞት አጣች፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም ከትናንት በስቲያ በትውልድ ስፍራቸውና የሱልጣንነት መቀመጫቸው በነበረችው አሳይታ ከተማ ተፈጽሟል፡፡

የአፋር ብሔረሰብ መንፈሳዊና ባህላዊ ፖለቲካዊም መሪ የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ በቀዳማዊ አፄ ኃይሌ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት (1923-1967) ከፍተኛ ሥልጣን ከነበራቸው መካከል አንዱ ነበሩ፡፡

በአፄ ኃይለ ሥላሴ የቢትወደድ ማዕርግ የተሰጣቸው ሱልጣን አሊሚራህ የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግሥትን በመቃወም በስደት በሳዑዲ ዓረቢያ በመኖር የአፋር ነፃ አውጭ ግንባርን ፡፡
ደርግ ከወደቀ በኋላ በ1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሽግግር መንግሥት በተመሠረተበት ጊዜ አንደኛው ተሳታፊ እንደነበሩም ይታወሳል፡፡
ሱልጣን ቢትወደድ አሊሚራህ ከሚጠቀስላቸው አነጋገራቸው፣ መካከል አንዱ ‹‹ግመሎቻችን ሳይቀሩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ያውቃሉ›› ያሉት ነው፡፡

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ሱልጣን አሊሚራህ በኢትዮጵያ ሽግግር መንግሥት (1983-87) በቀዳሚው ጉባኤ ላይ ‹‹ከጂቡቲ ጀምሮ እስከ ምፅዋ ድረስ በቆላው ምድር የሚኖረው የአፋር ሕዝብ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነን›› ማለታቸውም ይታወሳል፡፡

የ14 ወንድና የ15 ሴት ልጆች አባት የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ፣ ሚያዝያ 16 ቀን 2003 ዓ.ም. ማረፋቸው ከአፋር ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሥርዓተ ቀብራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ሹማምንትና የሃይማኖት መሪዎች ሌላ የጂቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ደሌታ መሐመድና የጂቡቲ የሃይማኖትና የጎሳ መሪዎች መገኘታቸው ታውቋል፡፡

Advertisement

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s