ቄሰ ገበዝ መሐመድ እና ሼክ መሐመድ ኃይለክርስቶስ

እኛ ኢትዮጵያውያን በዘመናዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኋላ ቀር ልንሆን እንችላለን፡፡ ነንም፡፡ በኢኮኖሚ ያላደግንና ያልበለፀግን ድሆች ልንሆን እንችላለን፡፡ ነንም፡፡ ምድባችንና ቦታችን ኋላ ቀር፣ ያልበለፀጉና ድሆች እየተባሉ ከሚመደቡ አገሮችና ሕዝቦች ውስጥ መሆናችንን እናውቃለን፡፡ አንቃወምም፡፡ አሜን ብለን እንቀበለዋለን፡፡

በምንም ይዘትና መልኩ የማንቀበለው ነገር ግን አለ፡፡ በባህል፣ በታሪክ፣ በሃይማኖት ኋላ ቀር ብሎ የሚያንቋሽሸንና የሚንቀንን የማንቀበል አገርና ሕዝብ ነን፡፡ የሚያኮራ ታሪክ፣ ባህልና ሃይማኖት አለን፡፡ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎችና በአንዳንድ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች አንድን ሃይማኖት ደግፎና አሞግሶ ሌላውን ሃይማኖት ተቃውሞ፣ አንኳሶና አሳንሶ የሚያስተጋባ ፅሁፍና መልዕክት ሲሰራጭ ታይቷል፡፡ አስፈላጊ ያልሆነ ግጭት ለመቀስቀስ ወረቀት እስከመበተንም ተደርሷል፡፡ Click to cont…