Tags

, , ,

የአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ሙሉ በሙሉ ተበተነ፡፡ አዲሱ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሁለት ወኪሎችንአቀረበ፡፡

በአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ኤሊያስ ሰኢድ ሰብሳቢነት በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዳራሽ ሰሞኑን በተካሄደ ስብሰባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ አባላት ሙሉ በሙሉ መበተናቸውን በስብሰባው የተሳተፉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል አደራጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለአንድ ወር ያህል ከወረዳ የምክር ቤቱ አባላት ጋር ውይይት በማድረግ አመራሮቹ ሙሉ በሙሉ መወገድ እንደለባቸው ሃሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት ጉባኤው የቀድሞውን አመራር በድክመት እንዲነሱ ሲወስን አዲስ የሥራ አስፈፃሚ አባላትንም እንደመረጠ ከተሳታፊዎቹ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በዚሁ መሠረት ሀጂ ባሀር አብደላ ሊቀመንበር፣ አቶ አማን ኢብራሂም ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ ሼክ ኤልያስ ሬድዋን ዋና ፀሀፊ ሆነዋል፡፡

አዲስ ከተመረጡት አስራ አንድ የስራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ሀጂ ኡመር እንድሪስና ሼህ ኑረዲን ይላል የአዲስ አበባን በመወከል ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች አመራርነት መወከላቸው ታውቋል፡፡ በስብሰባው የተሳተፉት እንደገለፁት ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሁለቱ አዲስ አባላት መወከላቸው ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ የተወከሉትን ውክልና ይሰራል፡፡

ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ ተወክለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ሼክ ኤሊያስ ሬድዋን እያሉ አዲስ ወኪሎችን መላክ ለቀድሞው ተወካይ ውክልና መንፈግ ማለት እንደሆነ ስለአሰራሩ የሚያውቁ ተናግረዋል፡፡ እንደ እነዚሁ ሰዎች ገለፃ ሼክ ኤሊያስ ያለውክልና በያዙት ኃላፊነት መቀጠል አይችሉም፡፡

ሼክ ኤሊያስን በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ ለማነጋገር ሞክረንወረቀቱ እስኪደርሰኝ እየጠበኩኝ ነውየሚል አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በምርጫ 97 ግርግር ምክንያት የስራ ዘመናቸው ባይራዘም የስራ ጊዜያቸውን የሚጨረሱት ከሦስት ዓመት በፊት ነበር፡፡

 

 

Advertisements