የጠራሁ  ሃበሻ  ባለቡና  ቀለም

ትምህርት ቤት ገባሁ ልጠቅም ሃገሬን

ከናቴ ተለየሁ ቀየርኩ እቤቴን

ለእውቀት ተስማሚም ምኖርበትን

ምወደውን ቦታ የምመኝውን

ከናት ቤት ወጥቼ ሌላ ቤት ስገባ

እኔስ መስሎኝ ነበር ሚሰጡኝ አበባ

ሀይማኖቴ የጥንት አይደለም አዲስ

አይደለም ከለሬ ጥቁር ወይ ድፍርስ

ወይም ነጭ አይደለሁ ወይ ሽንብራ ገብስ

የጠራሁ ሃበሻ ባለ ቡና ቀለም ኢትዮጵያዊት ሰው

የመለከቱኛል ጥላቻን አንግስው

በክብርም ቦታ ውርደትን ተክተው

ከቶም ሀሳብ ገባኝ አዲስ በመሆኔ

ምርጫዬ ጎድቷቸው ከቶ መሸፈኔ ?

ወይስ ሌላ ነገር ያላወኩት እኔ ?

ከቶም አዲስ አይደል ይህ የመሸፋፈኑ

በርግጥም ሀጽያትነው እራቁት ተሂዶ ፅጉር መቆነኑ

ሊኮነን ሚገባው ኢትዮጵያን ላጤኑ

ባህል ለሚያውቁ ለሚያስተነትኑ

በርግጥ ነግረኅኛል አንተ መምህሬ

ትምርት እንድጠላ ከሬትም አምርሬ

አልነበረም ከቶ መምህር ማለት

አንዱን ብቻ ወዶ ሌላውን መጥላት

በርግጥ ነበረ እንጂ ወገን አስታራቂ

የተማረ ማለት ችግሮችን ፈቶ ሁሉን አስደናቂ

በጥበብ አንጋሹ ለፍቅር ተጨናቂ

ከማንም ሳየወግን ፍትህን አርቃቂ

ከራሱ አስቀድሞ ለወገን ወዳቂ

ባመኑበት ሁሉን በትግስት ጠባቂ

ይህ ነበር እስካሁን እኔ እንደምረዳው

አስተማሪ ማለተ እኔ እስከማውቀው

ከቶ ተስፋ የለም ፍርድ ሳይሟላ

ሰው ወደፊት ሲሄድ እኛ ወደ ሁዋላ

ችኩሎች አንሁን ፍርድን ለማጉደል

ይህ ቀን ሳይለወጥ  ከቶ አይቀር በደል

ንግስናውን ጭኖ በህቴ ላይ ተንኮል

ለተቆጠበችው ክብሯ ለላቀባት

ፈጣሪንዋን ታዛዥ በምርጫዋ ሂደት

እንቅፋት አንሁን ይገባትም ክብረት

መሸፋፈን እኮ ለሷ ነው ድንቅ ውበት

ምላስም ይቆጠብ ምንናገርበት

የፍርድ ቀን ደርሶ ከምንጠየቅበት

ፍትህን እንውደድ ሀገር ታጊጥበት

ፍትህን እናብዛ ኢትዮጵያም ትኩራበት!!!

ይህ  መታሰብያነቱ  ለሁሉም  የዩኒቨርሲቲ  ሂጃቢት ተማሪ  እህቶቼ  ይሁን!!!images

    ሚዛናዊ ዜና በአማል