Tags

, , , , , ,

እንድያው አንድ ነገር ትዝ አለኝ እና እስኪ ልጫር ብዮ ብዕሬን አነሳሁ።  ጉዳዩ አሉኝ አንድ ሰው ዛሬ ግዜውን በትልክል በማላስታውስበት ወቅት ይላሉ እኝህ ሰው በአንድ ወቅት የሱዳኑ national Islamic Front መሪ የነበሩት ሃሰን አል-ቱራቢ ጋዜጠኞችን ሰብስበው ስለ ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ እያደረገችው በነበረው የድንበር ውጥረት ዙርያና እሱን ተከትሎ የመለስ መንግስ ስላደረጋቸው ጥቃቶች እንዲህ ገልጸው ነበር አሉኝ።  እኛ ኢትዮጵያ ለምን ጦርነት እንደከፈተችብን አናውቅም ሆኖም መሬት ፈልጋ ከሆነ ሱዳን ትልቅ ስለሆነች ቆርጠን እንሰጣለን ፣ አሜሪካም ይሁን ሌላ አቶ መለስ ሚገዙለት ሃገር ባጀት መድበውላቸው ከሆነ ባጀቱ እስከሚያልቅ ብንደበደብም እንታገሳለን ሆኖም ሱዳን እና ህዝቧን ለመምታት ፣ ለማጥቃት ታልሞ ከሆነ ግን መለስ የአያቱ እራስ ቅል ካርቱም እንደሚገኝ ሊያስታውስ ይገባዋል (አጼ-ዮሃንስን ለማለት ነው)።

ዛሬ ታድያ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞችም የተመደበው ባጀት እስኪያልቅ ይመስላል አህባሽንም ህገ-መንግስቱንም ጉሮሯችሁን ከፍተን እናንቆረቁርባቹሃለን እየተባሉ በተለያዩ መድረኮች እና የስብሰባ አዳራሾች በፌዴራል ጉዳዮች ጠመንጃ ታጅበው አህባሽን እየተጠመቁ ያሉት።  ሚዛናዊ ዜና ላይ ሰማን እንዳትሉ እንጂ ዶክተር ሽፈራው 10 ሚሊዮን ብር በግል አካውንታቸው እንደገባ በአዲስ አበባ ይወራል ይህን ሚስጥርም እንደሌሎች ሚስጥሮቻቸው ሁሉ ወዳጆቻቸው እሱ በልቶ ነው እንዲህ ሚሆነው እኔ ምን በወጣኝ የሚሉ የፌዴራል መስርያቤቱ ሰራተኞች በየዕለቱ ሚወያዩበት ጉዳይ እንደሆነ ውስጥ አዋቂ የሆኑት እኝህ ሰው አውግተውኛል።

ሌላው ባጀት እስኪያልቅ የሚደረግ ዘመቻ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ የማጥመቁ አባዜ መቸም በእርግጠኝነት እውነት ነው የሚያስብሉ ብዙ ገጽታዎች አሉት።  መቸም የሰው ልጅ በተፈጥሮው የኔናቸው የሚላቸውን እሴቶች ብሎም  እራሱን መውደዱ ጉዳይን ለማወቅ psychologist መሆን አይጠበቅብንም።    ታድያ መንግስት በምን መስፈርት ነው ሰዎች ያሏቸውን እሴቶች ጥለው እኔ በምፈልገው መንገድ እና አቅጣጫ ህዝብን አስኬደዋለሁ እምነቱንም ቢሆን በኔ ንድፍና ስርዓት እነዳዋለሁ ብሎ መድከሙ?  በፖለቲካ ፍልስፍና ይቻል ይሆናል በጊዚያዊነትም ቢሆን ታድያ ግን እምነትን ይቻላል ትላላችሁ ያውም ከህዝብ ድጋፍ የሌለው መንግስት? መቸም አንዳንዶች መንግስት ህዝብ ይደግፈዋል ብላቹ ምታስቡ ካላችሁ ምርጫ 97 በራሱ መልስ ስለሆነ በዛ ላይ ትንታኔ አልሰጥም እናንተንም ለማሳመን አልደክምም።  ግና ህገ-መንግስት በመስጅዶች መስጠት ማስተማሩ ምን ይሉታል እንድያው ህገ-መንግስት እያስተማርን ነው እንኳን ቢሉ?  ደግሞስ ዜጎች ሁሉ መማር አለባቸው ወይስ ሙስሊሞች ብቻ ? ምነው ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አይደለም ዜግነት ልትሰጡት አማራቹ?  እንዴ ከህገ-መንግስት class በሆዋላ ለላምን ልታመጡ ነው? መቸ ነው የቸርቹ ህገ-መንግስት class?  ወለተይ….አለች …  አዜብ…

ዶክተር ሰሞኑን የሰማሁትን ሚስጥር ላካፍሎት ሰዎች ሃይማኖታችንን ተከተሉ ብለው ሰዎችን ሲያስገድዱ ሰምተናል አንብበናል በታሪክ ሆኖም የሌላሰው እምነት ተቀበል ተብሎ የተነገረው ወይም የተገደደ በሰው ልጅ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ ድንቅ ታሪክ ሲሆን የአቶ መለስ መንግስት ደግሞ ይህን በማድረጉ የመጀመርያው ነው ለዚህ ስራ አስፈጻሚነት የተሾሙት ደግሞ እርስዎ ነዎት… ወይ phd አፈር በላው።   ዶክተር ሽፈራው እባኮን ወይ የበጀቱን መጠን ይንገሩን ወይም መልዕክት በጎን ያስተላልፋ ብዙ አይቆይም ብለው።  ምክንያቱም በእርግጠኝነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሙስሊሙ እርሶ ከሚገምቱት በላይ ለዕምነቱ ታጋይ ብቻ አይደለም በሳል እና አዋቂ ነው ስለሆነም አይሳካም ባይሆን ከተመደበው ባጀት ዘይት ይገዛና ለደሃው ህዝብ ይታደል ረሳሁ ስኳርም የለም የለም ምን እሱ ብቻ ምንም የለም ለካስ እሺ ገንዘቡ የቻለውን ያህል ይግዙበትና መልሱን keep ያርጉ አደራ ጉዳዩን አክስቴ አዜብ እንዳይሰሙ የገንዘብ ጉዳይ ሲነሳ ፓርቲያችን sensetive ነው።  ቸር እንሰንብት።

Advertisements